1 ለዐመፀኛዪቱና ለረከሰች፣ለጨቋኞች ከተማ ወዮላት!
2 እርሷ ለማንም አትታዘዝም፤የማንንም ዕርምት አትቀበልም፤ በእግዚአብሔር አትታመንም፤ወደ አምላኳም አትቀርብም።
3 ሹሞቿ የሚያገሡ አንበሶች፣ገዦቿ ለነገ የማይሉ፣የምሽት ተኵላዎች ናቸው።
4 ነቢያቷ ትዕቢተኞች፣አታላዮችም ናቸው፤ካህናቷ መቅደሱን ያረክሳሉ፣በሕግም ላይ ያምፃሉ።
5 በእርሷ ውስጥ ያለው እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ፈጽሞ አይሳሳትም፤በየማለዳው ቅን ፍርድ ይሰጣል፤በየቀኑም አይደክምም፤ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም።
6 “ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ምሽጋቸው ተደምስሶአል፤ማንም እንዳያልፍባቸው፣መንገዳቸውን ባድማ አደረግሁ፤ከተሞቻቸው ተደምስሰዋል፤አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም ከቶ አይገኝባቸውም።