4 ይህን ነገር በሰማሁ ጊዜ አያሌ ቀናት ዐዘንሁ፤ ጾምሁ፤ ጸለይሁም።
5 ከዚያም እንዲህ አልሁ፤“ለሚወዱህና ትእዛዝህን ለሚያከብሩ የፍቅርህን ቃል ኪዳን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምላክ፣ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤
6 ባሪያህ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤል ሕዝብ ቀንና ሌሊት በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ይንቃ፤ ዐይንህም ይከፈት። እኔንና የአባቴን ቤት ጨምሮ እኛ እስራኤላውያን አንተን በመበደል የሠራነውን ኀጢአት እናዘዛለሁ።
7 በአንተ ላይ እጅግ ክፉ ሥራ ሠርተናል፤ ለባሪያህም ለሙሴ የሰጠኸውን ትእዛዝ፣ ሥርዐትና ሕግ አልጠበቅንም።
8 “ለባሪያህ ለሙሴ እንዲህ ስትል የሰጠኸውን ቃል አስብ፤ ‘ታማኞች ካልሆናችሁ፣ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤
9 ወደ እኔ ብትመለሱና ትእዛዞቼን ብትፈጽሙ፣ የተሰደዱት ወገኖቻችሁ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ፣ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፤ ለስሜም ማደሪያ ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።’
10 “እነዚህም በታላቁ ኀይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባሪያዎችህና ሕዝብህ ናቸው።