8 በመያዣነት በተወሰደው ልብስ ላይ፣በየመሠዊያው ሥር ይተኛሉ፤በአምላካቸው ቤት፣በመቀጫነት የተወሰደውን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
9 ቁመቱ እንደ ዝግባ፣ጥንካሬውም እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረ ቢሆንም፣አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁት፣ከላይ ፍሬውን፣ከታችም ሥሩን አጠፋሁ።
10 “የአሞራውያንን ምድር ልሰጣችሁ፣ከግብፅ አወጣኋችሁ፤አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መራኋችሁ።
11 ደግሞም ነቢያትን ከወንዶች ልጆቻችሁ መካከል፣ናዝራውያንንም ከጐልማሶቻችሁ መካከል አስነሣሁ፤የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ ይህ እውነት አይደለምን?”ይላል እግዚአብሔር።
12 “እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ነቢያቱንም ትንቢት እንዳይናገሩ አዘዛችኋቸው።
13 “እነሆ፤ በእህል የተሞላ ጋሪ እንደሚያደቅ፣እኔም አደቃችኋለሁ።
14 ፈጣኑ አያመልጥም፤ብርቱውንም ብርታቱ አይረዳውም፤ኀያሉም ነፍሱን አያድንም።