አሞጽ 4:1-7 NASV

1 እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፣ድኾችን የምትጨቁኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን”የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፣

2 ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሎአል፤“እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበትትሩፋናችሁ እንኳ በዓሣ መንጠቆየሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል።

3 እያንዳንዳችሁ በቅጥሩ በተነደለው መሽሎኪያወደ ሬማንም ትጣላላችሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።

4 “ወደ ቤቴል ሂዱና ኀጢአትን ሥሩ፤ወደ ጌልገላም ሂዱና ኀጢአትን አብዙ፤በየማለዳው መሥዋዕቶቻችሁን፣በየሦስቱ ዓመት ዐሥራታችሁን አቅርቡ።

5 እርሾ ያለበትን እንጀራ የምሥጋናመሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ፤በፈቃዳችሁም በምታቀርቡት ቊርባን ተመኩ፤እናንት እስራኤላውያን በእነርሱም ተኵራሩ፤ ማድረግ የምትወዱት ይህን ነውና፤”ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

6 በየከተማው ሆዳችሁን ባዶ አደረግሁት፤በየመንደሩም የምትበሉትንአሳጣኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም”ይላል እግዚአብሔር።

7 “መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ዝናብ ከለከልኋችሁ፤በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብአደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ሌላው ዝናብ አጥቶ ደረቀ።