20 የእግዚአብሔር ቀን ብርሃን ሳይሆን ጨለማ፣የብርሃን ጸዳል የሌለው ድቅድቅ ጨለማ አይደለምን?
21 “ዓመት በዓላችሁን ተጸይፌአለሁ፤ጠልቼውማለሁ፤ ጉባኤዎቻችሁ ደስ አያሰኙኝም።
22 የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቊርባን ብታቀርቡልኝም፣እኔ አልቀበለውም፤ከሰቡ እንስሶቻችሁ የኅብረት መሥዋዕት ብታቀርቡልኝም፣እኔ አልመለከተውም።
23 የዝማሬህን ጩኸት ከእኔ አርቅ፤የበገናህንም ዜማ አልሰማም።
24 ነገር ግን ፍትሕ እንደ ወንዝ፣ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ።
25 “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣መሥዋዕትንና ቊርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?
26 ለራሳችሁ የሠራችሁትን፣የንጉሣችሁን ቤተ ጣዖት፣የጣዖቶቻችሁን ዐምድ፣የአምላካችሁን ኮከብ አንሥታችሁ ተሸከማችሁ።