4 እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት እንዲህይላል፤ “እኔን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።”
5 ቤቴልን አትፈልጉ፤ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤ጌልገላ በእርግጥ ትማረካለች፤ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና።
6 እግዚአብሔርን ፈልጉ፤በሕይወትም ትኖራላችሁ፤አለበለዚያ እንደ እሳት የዮሴፍን ቤት ያወድማል፤እሳቱም ቤቴልን ይበላል፤ የሚያጠፋውም የለም።
7 እናንት ፍትሕን ወደ መራርነት የምትለውጡ፣ጽድቅንም ወደ ምድር የምትጥሉ ወዮላችሁ!
8 ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስ፣ስሙ እግዚአብሔር ነው፤
9 እርሱ በብርቱው ላይ ድንገተኛ ጥፋትን፣በተመሸገውም ከተማ ላይ ውድመትን ያመጣል።
10 እናንተ በፍርድ አደባባይየሚገሥጻችሁን ትጠላላችሁ፤ እውነት የሚናገረውንም ትንቃላችሁ።