3 ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!
4 በዝሆን ጥርስ ባጌጠ ዐልጋ ላይ ለምትተኙ፤በድንክ ዐልጋችሁ ላይ ለምትዝናኑ፣ከበጎች መንጋ ጠቦትን፣ከጋጣም ጥጃን ለምትበሉ፤
5 ባልተቃኘ በገና ለምትዘፍኑ፣በሙዚቃ መሣሪያ ለመጫወት ለምትሹ፣
6 በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፣ምርጥ ሽቱም ለምትቀቡ፣ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ወዮላችሁ!
7 ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናቸሁ፤መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።
8 ጌታእግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ከተማዪቱንና በውስጥዋ ያለውን ሁሉ፣አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል፤ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
9 በአንድ ቤት ውስጥ ዐሥር ሰዎች ቢቀሩ እነርሱም ይሞታሉ።