1 ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤“መድረኮቹ እንዲናወጡ፣ጒልላቶቹን ምታ፣በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤ከእነርሱ አንድም ሰው አይሸሽም፤ቢሸሽም የሚያመልጥ የለም።
2 መቃብር በጥልቀት ቈፍረው ቢወርዱም፣እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ወደ ሰማይ ቢወጡም፣ከዚያ አወርዳቸዋለሁ።
3 በቀርሜሎስ ጫፍ ላይ ቢሸሸጉም፣አድኜ ፈልጌ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤እይዛቸዋለሁም፤በጥልቅ ባሕር ውስጥ ከእኔ ቢሸሸጉም፣በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ፤
4 በጠላቶቻቸው ተነድተው ለምርኮ ቢወሰዱም፣በዚያ እንዲገድላቸው ሰይፍን አዛለሁ፤ለመልካም ሳይሆን ለክፉ፣ዓይኔን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ።