3 በቀርሜሎስ ጫፍ ላይ ቢሸሸጉም፣አድኜ ፈልጌ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤እይዛቸዋለሁም፤በጥልቅ ባሕር ውስጥ ከእኔ ቢሸሸጉም፣በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ፤
4 በጠላቶቻቸው ተነድተው ለምርኮ ቢወሰዱም፣በዚያ እንዲገድላቸው ሰይፍን አዛለሁ፤ለመልካም ሳይሆን ለክፉ፣ዓይኔን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ።
5 ጌታ፣ እግዚአብሔር ጸባኦት፣ምድርን ይዳስሳል፤እርሷም ትቀልጣለች፤በውስጥዋ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤የምድር ሁለመና እንደ ዐባይ ወንዝ ይነሣል፤እንደ ግብጽ ወንዝም ይወርዳል።
6 መኖሪያውን በሰማይ የሚሠራ፣መሠረቱንም በምድር የሚያደርግ፣የባሕርን ውሃ የሚጠራ፣በምድርም ገጽ ላይ የሚያፈስ፣እርሱ ስሙ እግዚአብሔር ነው።
7 “እናንት እስራኤላውያን፣ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?”ይላል እግዚአብሔር“እስራኤልን ከግብጽ፣ፍልስጥኤማውያንን ከከፍቶር፣ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?
8 “እነሆ፤ የጌታ እግዚአብሔር ዐይኖች፣በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤ከምድር ገጽ፣ ፈጽሜ አጠፋዋለሁ፤የያዕቆብን ቤት ግን፣ ሙሉ በሙሉአልደመስስም፤”ይላል እግዚአብሔር።
9 “እነሆ፤ ትእዛዝ እሰጣለሁ፤እህል በወንፊት እንደሚነፋ፣የእስራኤልን ቤት፣በሕዝብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።