6 መኖሪያውን በሰማይ የሚሠራ፣መሠረቱንም በምድር የሚያደርግ፣የባሕርን ውሃ የሚጠራ፣በምድርም ገጽ ላይ የሚያፈስ፣እርሱ ስሙ እግዚአብሔር ነው።
7 “እናንት እስራኤላውያን፣ለእኔ እንደ ኢትዮጵያውያን አይደላችሁምን?”ይላል እግዚአብሔር“እስራኤልን ከግብጽ፣ፍልስጥኤማውያንን ከከፍቶር፣ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?
8 “እነሆ፤ የጌታ እግዚአብሔር ዐይኖች፣በኀጢአተኛ መንግሥት ላይ ናቸው፤ከምድር ገጽ፣ ፈጽሜ አጠፋዋለሁ፤የያዕቆብን ቤት ግን፣ ሙሉ በሙሉአልደመስስም፤”ይላል እግዚአብሔር።
9 “እነሆ፤ ትእዛዝ እሰጣለሁ፤እህል በወንፊት እንደሚነፋ፣የእስራኤልን ቤት፣በሕዝብ ሁሉ መካከል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም።
10 በሕዝቤ መካከል ያሉ፣‘ክፉ ነገር አያገኘንም ወይም አይደርስብንም’ የሚሉ፣ኀጢአተኞች ሁሉ፣በሰይፍ ይሞታሉ።
11 “በዚያ ቀን፣የወደቀውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ፤የተሰበረውን እጠግናለሁ፤የፈረሰውን ዐድሳለሁ፤ቀድሞ እንደነበረም አድርጌ እሠራዋለሁ፤
12 ስለዚህ የኤዶምን ትሩፍ፣በስሜ የተጠሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ይወርሳሉ፤”ይላል ይህን የሚያደርግ እግዚአብሔር።