1 ደግሞም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆ፤ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰውም በፊቴ አየሁ፤
2 እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው?” አልሁት።እርሱም፣ “የኢየሩሳሌም ርዝመትና ስፋትምን ያህል እንደሆነ ለመለካት መሄዴ ነው” አለኝ።
3 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ፤
4 እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጒልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤
5 እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር ‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’
6 “ኑ! ኑ! ውጡ ከሰሜን ምድር አምልጡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለአራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።
7 “አንቺ ጽዮን ነዪ፤ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፤ ኰብልዪ።”