3 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ፤
4 እንዲህም አለው፣ “ሩጥና ለዚያ ጒልማሳ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘በውስጧ ካለው የሰውና የከብት ብዛት የተነሣ፣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች፤
5 እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር ‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’
6 “ኑ! ኑ! ውጡ ከሰሜን ምድር አምልጡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለአራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።
7 “አንቺ ጽዮን ነዪ፤ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፤ ኰብልዪ።”
8 እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላልና፤ “ካከበረኝና በዘረፉአችሁ አሕዛብ ላይ ከላከኝ በኋላ፣ የሚነካችሁ የዐይኑን ብሌን ይነካል፤
9 እነሆ፤ እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል፤ ከዚያም እግዚአብሔር ጸባኦት እኔን እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።