3 ደግሞም አንዱ ከዘይቱ ማሰሮ በስተ ቀኝ፣ ሌላውም በስተ ግራ የሆኑ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”
4 ያነጋግረኝ የነበረውንም መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እነዚህ ምንድን ናቸው” አልሁት።
5 እርሱም፣ “ምን እንደሆኑ አታውቅምን?” አለኝ።እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፤ አላውቅም” አልሁት።
6 ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የተላከው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ በኀይልና በብርታት አይደለም’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።
7 “ታላቅ ተራራ ሆይ፤ አንተ ምንድን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች፣ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ፣ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።”
8 ደግሞም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤
9 “የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤተ መቅደስ መሠረት ጣሉ፤ የሚፈጽሙትም የእርሱ እጆች ናቸው። ከዚያም እግዚአብሔር ጸባኦት እኔን ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።