ዘዳግም 11:23-29 NASV

23 ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፣ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ።

24 በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፣ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል።

25 ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማስደንገጣችሁንና መፈራታችሁን በምትሄዱበት በየትኛውም ምድር ሁሉ ላይ ያሳድራል።

26 እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤

27 በረከቱ ዛሬ የምሰጣችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትእዛዞች ስትፈጽሙ ሲሆን፣

28 መርገሙ ደግሞ፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትእዛዞች የማትፈጽሙ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።

29 ልትወርሳት ወደ ምትሄድባት ምድር አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፣ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ።