29 የምትወሯቸውንና የምታስለቅቋቸውን አሕዛብ አምላካችሁ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከፊታችሁ ያስወግዳቸዋል፤ ባስወጣችኋቸውና በምድራቸው በተቀመጣችሁ ጊዜ ግን፣
30 ከፊትህ ከጠፉ በኋላ፣ “እነዚህ ሕዝቦች አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እኔም እንደ እነርሱ አደርጋለሁ” ብለህ በመጠየቅ እንዳ ትጠመድ ተጠንቀቅ።
31 አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በእነርሱ መንገድ ፈጽሞ አታምልክ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን ሲያመልኩ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚጸየፈውን ሁሉንም ዐይነት ነገር ያደርጋሉና፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን እንኳ ለአማልክታቸው መሥዋዕት አድርገው ያቃጥላሉ።
32 እኔ ያዘዝሁህን ሁሉ ጠብቅ፤ አትጨምር በት፤ አትቀንስለትም።