19 የቀንድ ከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎችህን ተባዕት በኵር ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ቀድስ። የበሬህን በኵር አትሥራበት፤ የበግህንም በኵር አትሸልት፤
20 እርሱ በሚመርጠው ስፍራ አንተና ቤተ ሰብህ በየዓመቱ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ትበሉታላችሁ።
21 አንድ እንስሳ እንከን ካለበት፣ አንካሳ ወይም ዕውር፣ ወይም ደግሞ ማናቸውም ዐይነት ከባድ ጒድለት ያለበት ከሆነ፣ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አትሠዋው፤
22 በየከተሞችህም ትበላዋለህ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነውም ሆነ ያልሆነው ሰው፣ እንደ ድኵላ እንደ ዋላ ይበላዋል።
23 ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።