5 በእግዚአብሔር (ያህዌ) ስም ቆሞ ለዘላለም ያገለግል ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ከነገዶችህ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል።
6 አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በእስራኤል ካሉት ከተሞችህ መካከል በፍጹም ፈቃድ እግዚአብሔር (ያህዌ) ወደሚመርጠው ስፍራ ቢመጣ፣
7 በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ፣ እርሱም በአምላኩበእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ስም ያገልግል።
8 ከቤተ ሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳ፣ ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።
9 አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፣ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል።
10 በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ ሟርተኛ፣ ወይም መተተኛ፣ ሞራ ገለጭ፣ ጠንቋይ
11 ወይም በድግምት የሚጠነቍል፤ መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከልህ ከቶ አይገኝ።