1 ሰማያት ሆይ፤ አድምጡ፤ እኔም እናገራለሁ፤ምድር ሆይ፤ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ።
2 ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትውረድ፤ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፣ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ።
3 እኔ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም ዐውጃለሁ፤የአምላካችንን (ኤሎሂም) ታላቅነት አወድሱ!
4 እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም (ኤሎሂም) እርሱ ነው።
5 በእርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል፤ ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም፤ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው።