33 ወይናቸው የእባብ መርዝ፣የመራዥ እባብም መርዝ ነው።
34 “ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፣በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?
35 በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤የመጥፊያቸው ቀን ቀርቦአል፤የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።”
36 ኀይላቸው መድከሙን፣ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ለአገልጋዮቹም ይራራል።
37 እንዲህም ይላል፤ “መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፣እነዚያ አማልክታቸው የት አሉ?
38 የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፣የመጠጥ ቊርባናቸውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው?እስቲ ይነሡና ይርዷችሁ!እስቲ መጠለያ ይስጧችሁ!
39 “እኔ ራሴ እርሱ እንደሆንሁ እዩ፤ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤እገድላለሁ፤ አድናለሁም፤አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።