1 ሙሴ እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “እስራኤል ሆይ፤ በዛሬዋ ዕለት በጆሮአችሁ የምነግራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ አጥኗቸው፤ በጥንቃቄም ጠብቋቸው።
2 አምላካችን እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ገብቶአል።
3 እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን የገባውም ከአባቶቻችን ጋር ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ በሕይወት ከምንገኘው ከእኛ ከሁላችን ጋር ነው።
4 እግዚአብሔር (ያህዌ) እናንተን በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ፊት ለፊት አነጋገራችሁ።