ዘዳግም 5:10-16 NASV

10 ለሚወዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ ግን እስከ ሺህ ትውልድ ቸርነትንና ፍቅርን እገልጣለሁ።

11 “እግዚአብሔር (ያህዌ) ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሳይቀጣው አይቀርምና፤ የአምላክህንየእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ስም በከንቱ አታንሣ።

12 “አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ባዘዘህ መሠረት የሰንበትን ቀን ቀድሰህ አክብረው።

13 ስድስት ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን።

14 ሰባተኛው ቀን ግን የአምላክህ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ሰንበት ነው። በዚህም ቀን አንተም ሆንህ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህም ሆነ ሴት አገልጋይህ በሬህ፣ አህያህ ወይም ማናቸውም እንሰሳህ፣ ወይም ደግሞ በደጅህ ያለ እንግዳ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩ። ይህም አንተ እንዳረፍህ ሁሉ ወንድ አገልጋይህም ሆነ ሴት አገልጋይህ እንዲያርፉ ነው።

15 በግብፅ ሳለህ አንተም ባሪያ እንደ ነበርህ፣ ከዚያም አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ እንዳወጣህ አስታውስ፤ ስለዚህ አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሰንበትን ቀን ታከብረው ዘንድ አዘዘህ።

16 “አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር።