3 እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን የገባውም ከአባቶቻችን ጋር ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ በሕይወት ከምንገኘው ከእኛ ከሁላችን ጋር ነው።
4 እግዚአብሔር (ያህዌ) እናንተን በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ፊት ለፊት አነጋገራችሁ።
5 እናንተ ግን እሳቱን በመፍራት ወደ ተራራው ስላል ወጣችሁ፣ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ቃል ለእናንተ እነግራችሁ ዘንድ እኔ በእግዚአብሔርና (ያህዌ) በእናንተ መካከል ቆምሁ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤
6 “ከባርነት ምድር፣ ከግብፅ ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እኔ ነኝ።
7 “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።
8 በላይ በሰማይ፣ በታች በምድር ላይ፣ ባለው ወይም ከምድር በታች ውሃ ውስጥ በሚኖር በማንኛውም ዐይነት ምስል ለራስህ ጣዖትን አታብጅ፤
9 እኔ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ)፣ የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። ለእነርሱ አትስገድላቸው፤ ወይም አታምልካቸው።