22 እኛ በዐይናችን እያየን እግዚአብሔር (ያህዌ) ታላላቅና አስፈሪ የሆኑ ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆችን በግብፅ፣ በፈርዖንና በመላው ቤተ ሰዎቹ ላይ አደረገ።
23 እኛን ግን ለአባቶቻችን በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ሊያስገባንና ሊሰጠን ከዚያ አወጣን።
24 ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ምንጊዜም መልካም እንዲሆንልንና በሕይወት እንድንኖር ይህን ሥርዐት ሁሉ እንድንፈጽም፣ አምላካችንንምእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) እንድንፈራ እግዚአብሔር (ያህዌ) አዘዘን።
25 እንግዲህ ይህን ሁሉ ሕግ እርሱ ባዘዘን መሠረት፣ በአምላካችንበእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ተጠንቅቀን ከጠበቅን፣ ያ ለእኛ ጽድቃችን ይሆናል።”