ዘዳግም 8:13-19 NASV

13 ደግሞም የከብት፣ የበግና የፍየል መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበረክት፣ ያለህም ሁሉ በላይ በላዩ እየጨመረ ሲሄድ፣

14 ልብህ ይታበይና ከባርነት ምድር፣ ከግብፅ ያወጣህን አምላክህንእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትረሳለህ።

15 በዚያ ጭልጥ ባለና አስፈሪ ምድረ በዳ፣ በዚያ በሚያስጠማና ውሃ በማይገኝበት ደረቅ መሬት፣ መርዘኛ እባብና ጊንጥ ባለበት ምድረ በዳ መራህ፤ ከጽኑ ዐለትም ውሃ አፈለቀልህ።

16 በመጨረሻ መልካም እንዲሆንልህ፣ አንተን ትሑት ለማድረግና ለመፈተን፣ አባቶችህ ፈጽሞ የማያውቁትን መና በምድረ በዳ መገበህ።

17 ምናልባትም፣ “ይህን ሀብት ያፈራሁት በጒልበቴና በእጄ ብርታት ነው” ብለህ በልብህ ታስብ ይሆናል።

18 ነገር ግን ሀብት እንድታፈራ ችሎታ የሰጠህ፣ ለአባቶችህም በመሐላ የገባውን ኪዳን ያጸናልህ እርሱ ስለ ሆነ፣ አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) አስበው።

19 አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ብትረሳና ሌሎችን አማልክት ብትከተል፣ ብታመልክና ለእነርሱ ብትሰግድላቸው በእርግጥ እንደምትጠፉ ዛሬ እመሰክርባችኋለሁ።