ዳንኤል 6:23-28 NASV

23 ንጉሡ እጅግ ተደስቶ፤ ዳንኤልን ከጒድጓዱ እንዲያወጡት አዘዘ። ዳንኤል በአምላኩ ታምኖ ነበርና ከጒድጓድ በወጣ ጊዜ፣ አንዳች ጉዳት አልተገኘበትም።

24 በንጉሡ ትእዛዝ፣ ዳንኤልን በሐሰት የከሰሱትን ሰዎች፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር አምጥተው፣ በአንበሶቹ ጒድጓድ ውስጥ ጣሏቸው፤ ገና ወደ ጒድጓዱ መጨረሻ ሳይደርሱም፣ አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ ዐጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።

25 ከዚያ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ፣ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝቦች፣ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ሰዎች ሁሉ እንዲህ የሚል መልእክት ጻፈ፤“ሰላም ይብዛላችሁ!

26 “በማንኛውም የመንግሥቴ ግዛት ሰው ሁሉ፣ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር ይህን ዐዋጅ አውጥቻለሁ።“እርሱ ለዘላለም የሚኖር፣ሕያው አምላክ ነውና፣መንግሥቱ አይጠፋም፤ለግዛቱም መጨረሻ የለውም።

27 እርሱ ይታደጋል፤ ያድናልም፤በሰማይና በምድር፣ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋል፤ዳንኤልን፣ከአንበሶች አፍ አድኖታል።”

28 ስለዚህ ዳንኤል በዳርዮስ ዘመነ መንግሥትና በፋርሳዊው በቂሮስ ዘመነ መንግሥት ሁሉ ኑሮው ተሳካለት።