4 የእኔ መሄድ የሚያስፈልግ ከሆነ አብረውኝ ይሄዳሉ።
5 በመቄዶንያ በኩል ማለፌ ስለማይቀር፣ መቄዶንያ ከደረስሁ በኋላ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
6 ወደምሄድበት ወደ ማናቸውም ስፍራ በጒዞዬ እንድትረዱኝ፣ እናንተ ዘንድ እቈይ ይሆናል፤ ምናልባትም ክረምቱን ከእናንተ ጋር እሰነብት ይሆናል።
7 አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጐበኛችሁ አልፈልግም፤ ጌታ ቢፈቅድ ረዘም ላለ ጊዜ እናንተ ዘንድ ለመሰንበት ተስፋ አደርጋለሁ።
8 ነገር ግን እስከ በዓለ ኀምሳ በኤፌሶን እቈያለሁ፤
9 ምክንያቱም ታላቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል፤ ብዙ ተቃዋሚዎችም አሉብኝ።
10 ጢሞቴዎስ ወደ እናንተ ከመጣ፣ አብሮአችሁ ያለ ፍርሀት እንዲቀመጥ አድርጉ፤ እርሱም እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና።