ሐዋርያት ሥራ 1:18-24 NASV

18 ይህ ሰው ስለ ክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ፤ በዚያም በግንባሩ ተደፍቶ ሰውነቱ እመካከሉ ላይ ፈነዳ፤ ሆድ ዕቃውም ተዘረገፈ፤

19 ይህም በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ መሬቱም በቋንቋቸው ‘አኬልዳማ’ ተብሎ ተጠራ፤ ትርጓሜውም ‘የደም መሬት’ ማለት ነው።

20 ጴጥሮስም በመቀጠል እንዲህ አለ፤“በመዝሙር መጽሐፍ፣‘መኖሪያው ባዶ ትሁን፤የሚኖርባትም ሰው አይገኝ’ ደግሞም፣‘ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፎአል።

21 ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በመካከላችን በገባበትና በወጣበት ጊዜ ሁሉ፣ ከእኛ ጋር ከነበሩት መካከል አንድ ሰው መምረጥ ያስፈልጋል፤

22 ይኸውም፣ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ ተለይቶ እስካረገበት ቀን ድረስ የነበረ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”

23 ስለዚህ ኢዮስጦስ የሚሉትን፣ በርስያን የተባለውን ዮሴፍንና ማቲያስን ሁለቱን አቀረቡ፤

24 እንዲህም ብለው ጸለዩ፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተ የሰውን ሁሉ ልብ ታውቃለህ፤ ከእነዚህ ከሁለቱ መካከል የመረጥኸውን ሰው አመልክተንና