9 “ያም ድምፅ ዳግመኛ፣ ‘እግዚአብሔር ንጹሕ ያደረገውን አንተ እንደ ርኩስ አትቍጠረው’ ሲል ከሰማይ ተናገረኝ።
10 ይህም ሦስት ጊዜ ተደጋገመ፤ ከዚያ ሁሉም እንደ ገና ወደ ሰማይ ተወሰደ።
11 “ልክ በዚያው ሰዓት፣ ሦስት ሰዎች ከቂሳርያ ወደ እኔ ተልከው መጥተው እኔ ባለሁበት ቤት ደጅ ላይ ቆሙ፤
12 መንፈስ ቅዱስም ምንም ሳላወላውል ከእነርሱ ጋር እንድሄድ ነገረኝ። እነዚህም ስድስት ወንድሞች ከእኔ ጋር ሄዱ፤ ወደ ሰውየውም ቤት ገባን።
13 እርሱም መልአክ በቤቱ ውስጥ ቆሞ እንደ ታየውና እንዲህ እንዳለው ነገረን፤ ‘ወደ ኢዮጴ ሰው ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስጠራ፤
14 እርሱም አንተና የቤትህ ሰዎች ሁሉ የምትድኑበትን ቃል ይነግርሃል።’
15 “እኔም ገና መናገር ስጀምር፣ መንፈስ ቅዱስ፣ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደ ወረደ ሁሉ በእነርሱም ላይ ወረደ።