35 ሲነጋም፣ ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ፈተህ ልቀቃቸው” ብለው መኰንኖቻቸውን ላኩበት።
36 የወህኒ ቤት ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ አዘዋል፤ ስለዚህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው።
37 ጳውሎስ ግን፣ “እኛ የሮም ዜጎች ሆነን ሳለን፣ በሕዝብ ፊት ያለ ፍርድ ደብድበው ወደ እስር ቤት ወረወሩን፤ ታዲያ አሁን በስውር ሊያስወጡን ይፈልጋሉ? ይህማ አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” አላቸው።
38 መኰንኖቹም ይህንኑ ቃል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ እነርሱም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ደነገጡ፤
39 እነርሱ ራሳቸውም መጥተው ይቅርታ ጠይቀው ከወህኒ ቤቱ አወጧቸው፤ ከተማውንም ለቀው እንዲሄዱ ለመኗቸው።
40 ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤቱ ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ሄዱ፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተው አበረታቷችው፤ ከዚያም በኋላ ሄዱ።