1 ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፣ ከጸሓፍትና ከመላው የሸንጎ አባላት ጋር ወዲያው ከተማከሩ በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱት፤ ለጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።
2 ጲላጦስም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ጠየቀው፤ ኢየሱስም፣ “አንተው አልኸው፣” በማለት መለሰለት።
3 የካህናት አለቆችም በብዙ ነገር ከሰሱት።
4 ጲላጦስም፣ “ለምን መልስ አትሰጥም? እነሆ በብዙ ነገር ከሰውሃል” ሲል እንደ ገና ጠየቀው።