1 በሌላ ጊዜ ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር።
2 በምክንያት ሊከሱት የሚፈልጉ ሰዎችም በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደሆነ ለማየት ይጠባበቁ ነበር።
3 እርሱም እጁ የሰለለችውን ሰው፣ “በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት ተነሥተህ ቁም” አለው።
4 ኢየሱስም፣ “በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” አላቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ።