13 ቀረፋ፣ ቅመም፣ ከርቤ፣ ቅባት፣ ዕጣን፣ የወይን ጠጅ፣ የወይራ ዘይት፣ የተሰለቀ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ከብቶች፣ በጎች፣ ፈረሶች፣ ሠረገሎች፣ እንዲሁም ባሮችና የሰዎች ነፍሶች ነው።
14 እነርሱም፣ ‘የተመኘሽው ፍሬ ከአንቺ ርቆአል፤ ብልጽግናሽና ክብርሽ ሁሉ ጠፍቶአል፤ ዳግመኛም ተመልሶ አይመጣም” ይላሉ።
15 እነዚህን ነገሮች በመሸጥ በእርሷ የበለጸጉ ነጋዴዎች ሥቃይዋን ፈርተው በሩቅ ይቆማሉ፤ እነርሱም ያለቅሳሉ፤ ያዝናሉም፤
16 ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲህ ይላሉ፤“ቀጭን የተልባ እግር፣ ሐምራዊና ቀይ ልብስ የለበሰች፣በወርቅ፣ በከበረ ድንጋይና በዕንቍም ያጌጠች፣ታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት!
17 ያ ሁሉ ሀብት በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፋ።”“የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞች ሁሉ፣ የመርከብ ሠራተኞችና ኑሮአቸውን በባሕር ላይ የመሠረቱ ሁሉ በሩቅ ይቆማሉ።
18 እርሷ ስትቃጠል የሚወጣውን ጢስ ሲያዩ፣ ‘እንደዚች ያለ ታላቅ ከተማ ከቶ የት አለ?’ እያሉ ይጮኻሉ።
19 በራሳቸውም ላይ አቧራ ነስንሰው እያለ ቀሱና እያዘኑ እንዲህ ብለው ጮኹ፤“ ‘በባሕር ላይ መርከቦች ያላቸው ሁሉ፣በእርሷም ሀብት የበለጸጉ፣ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት! ወዮላት!በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፍታለች።