1 በጉ ሰባተኛውን ማኅተም በፈታ ጊዜ፣ ግማሽ ሰዓት ያህል በሰማይ ዝምታ ሆነ።
2 ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፤ ሰባት መለከትም ተሰጣቸው።
3 ሌላም መልአክ የወርቅ ጥና ይዞ መጣና በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ እርሱም በዙፋኑ ፊት ባለው የወርቅ መሠዊያ ላይ ከቅዱሳን ጸሎት ሁሉ ጋር እንዲያቀርበው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።
4 የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ።