8 ጠጒራቸው የሴት ጠጒር፣ ጥርሳቸውም የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር።
9 የብረት ጥሩር የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የክንፎቻቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት የሚገሠግሡ የብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ድምፅ ይመስል ነበር።
10 እንደ ጊንጥም ያለ ጅራትና መንደፊያ ነበራቸው፤ ደግሞም ሰዎችን አምስት ወር የሚያሠቃዩበት ኀይል በጅራታቸው ላይ ነበር።
11 በላያቸው ንጉሥ ነበራቸው፤ እርሱም የጥልቁ ጒድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ “አብዶን”፣ በግሪክ ደግሞ “አጶልዮን” ይባላል።
12 የመጀመሪያው ወዮ ዐልፎአል፤ እነሆ፤ ከዚህ በኋላ ገና ሌላ ሁለት ወዮዎች ይመጣሉ።
13 ስድስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእግዚአብሔር ፊት ካለው በወርቅ ከተሠራው መሠዊያ ቀንዶች ድምፅ ሲመጣ ሰማሁ፤
14 ድምፁም መለከት የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ፣ “በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው” አለው።