ዕብራውያን 8:4-10 NASV

4 እርሱ በምድር ቢኖር ኖሮ ካህን ባልሆነም ነበር፤ ምክንያቱም በሕግ በታዘዘው መሠረት መባን የሚያቀርቡ ሰዎች አሉ።

5 እነርሱ ያገለገሉት በሰማይ ላለችው መቅደስ ምሳሌና ጥላ በሆነችው ውስጥ ነው፤ ሙሴ ድንኳኒቱን ለመሥራት በተነሣ ጊዜ፣ “በተራራው ላይ በተገለጠልህ ምሳሌ መሠረት ሁሉን ነገር እንድታደርግ ተጠንቀቅ” የሚል ትእዛዝ የተሰጠው በዚህ ምክንያት ነበር።

6 ነገር ግን ኢየሱስ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን ከቀድሞው እንደሚበልጥ ሁሉ፣ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፤ ይህም የተመሠረተው በተሻለ የተስፋ ቃል ላይ ነው።

7 የመጀመሪያው ኪዳን ምንም ጒድለት ባይገኝበት ኖሮ፣ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር።

8 ነገር ግን እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ጒድለት በማግኘቱ እንዲህ ይላቸዋል፤“ከእስራኤል ቤት ጋር፣ከይሁዳም ቤት ጋር፣አዲስ ኪዳን የምገባበት፣ጊዜ ይመጣል፤ ይላል ጌታ።

9 ይህም እነርሱን ከግብፅ ምድርለማውጣት እጃቸውን በያዝሁ ጊዜ፣ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ኪዳን አይደለም፤ምክንያቱም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑም፤እኔም ከእነርሱ ዘወር አልሁ፤ይላል ጌታ።

10 ከዚያን ጊዜ በኋላ፣ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ሕጌን በአእምሮአችው አኖራለሁ፤በልባቸውም እጽፈዋለሁ።እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።