ዕብራውያን 8:6-12 NASV

6 ነገር ግን ኢየሱስ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን ከቀድሞው እንደሚበልጥ ሁሉ፣ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፤ ይህም የተመሠረተው በተሻለ የተስፋ ቃል ላይ ነው።

7 የመጀመሪያው ኪዳን ምንም ጒድለት ባይገኝበት ኖሮ፣ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር።

8 ነገር ግን እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ጒድለት በማግኘቱ እንዲህ ይላቸዋል፤“ከእስራኤል ቤት ጋር፣ከይሁዳም ቤት ጋር፣አዲስ ኪዳን የምገባበት፣ጊዜ ይመጣል፤ ይላል ጌታ።

9 ይህም እነርሱን ከግብፅ ምድርለማውጣት እጃቸውን በያዝሁ ጊዜ፣ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ኪዳን አይደለም፤ምክንያቱም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑም፤እኔም ከእነርሱ ዘወር አልሁ፤ይላል ጌታ።

10 ከዚያን ጊዜ በኋላ፣ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ሕጌን በአእምሮአችው አኖራለሁ፤በልባቸውም እጽፈዋለሁ።እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

11 ከእንግዲህ ማንም ሰው ጐረቤቱንወይም ወንድሙን፣ ‘ጌታን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ምክንያቱም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ፣ሁሉም ያውቁኛል።

12 በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንከእንግዲህ አላስብም።”