7 የሰው ጥረት ሁሉ ለአፉ ነው፤ፍላጎቱ ግን ፈጽሞ አይረካም።
8 ጠቢብ ከሞኝ ይልቅ ምን ብልጫ አለው?ድኻስ በሌሎች ፊት እንዴት እንደሚኖር በማወቁ፣ትርፉ ምንድን ነው?
9 በምኞት ከመቅበዝበዝ፣በዐይን ማየት ይሻላል፤ይህም ደግሞ ከንቱ፣ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
10 አሁን ያለው ሁሉ አስቀድሞ ስም የተሰጠው ነው፤ሰው የሚሆነውም አስቀድሞ የታወቀ ነው፤ከራሱ ይልቅ ከሚበረታ ጋር፣ማንም አይታገልም።
11 ቃል በበዛ ቊጥር፤ከንቱነት ይበዛል፤ይህ ታዲያ ለሰው ምን ይጠቅማል?
12 ሰው በሕይወት ሳለ፣ እንደ ጥላ በሚያልፉት ጥቂትና ከንቱ በሆኑት ቀኖቹ፣ ለሰው መልካም የሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? እርሱ ከሄደ በኋላስ ከፀሓይ በታች የሚሆነውን ማን ሊነግረው ይችላል?