10 በጌት አታውሩት፤ከቶም አታልቅሱ፤በቤትዓፍራ፣በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።
11 እናንት በሻፊር የምትኖሩ፣ዕርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ዕለፉ፤በጸዓናን የሚኖሩከዚያ አይወጡም፤ቤትዔጼል በሐዘን ላይ ናት፤ለእናንተም መጠጊያ ልትሆን አትችልም።
12 ከመከራው መገላገልን በመሻት፣በማሮት የሚኖሩ በሥቃይይወራጫሉ፤እስከ ኢየሩሳሌም በር ሳይቀር፣ክፉ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአልና።
13 እናንት በለኪሶ የምትኖሩ፣ፈረሶችን ከሠረገላው ጋር አያይዙ፤ለጽዮን ሴት ልጅ፣የኀጢአት መጀመሪያ እናንት ነበራችሁ፤የእስራኤል በደልበእናንተ ዘንድ ተገኝቶአልና።
14 ስለዚህ እናንተ ለሞሬሼትጌት፣ማጫ ትሰጣላችሁ፤የአክዚብ ከተማ፣ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ትሆናለች።
15 እናንት በመሪሳ የምትኖሩድል አድራጊ አመጣባችኋለሁ፤ያ የእስራኤል ክብር የሆነውወደ ዓዶላም ይመጣል።
16 ደስ ለምትሰኙባቸው ልጆቻችሁ፣በሐዘን ራሳችሁን ተላጩ፤ራሳችሁን እንደ አሞራ ራስ ተመለጡት፤ከእናንተ በምርኮ ይወሰዳሉና።