10 ደግሞም መልአኩ፣ “ዘርሽን እጅግ አበዛለሁ፤ ከብዛቱም የተነሣ ሊቈጠር አይችልም” አላት።
11 የእግዚአብሔርም (ያህዌ) መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤“እነሆ፤ ፀንሰሻል፤ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ችግርሽን ተመልክቶአል፤ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ።
12 እርሱም እንደ ዱር አህያ ይሆናል፤እጁንም ባገኘው ሰው ሁሉ ላይ ያነሣል፤ያገኘውም ሁሉ እጁን ያነሣበታል፤ከወንድሞቹ ሁሉ ጋር እንደ ተጣላ ይኖራል።”
13 እርሷም ያናገራትን እግዚአብሔርን (ያህዌ)፣ ኤልሮኢ ብላ ጠራችው፤ ምክንያቱም “የሚያየኝን አሁን አየሁት” ብላ ነበርና።
14 ከዚህ የተነሣ የዚያ ምንጭ ስም፣ “ብኤርለሃይሮኢ” ተብሎ ተጠራ፤ እስካሁንም በቃዴስና በባሬድ መካከል ይገኛል።
15 አጋር ለአብራም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ አብራምም ስሙን እስማኤል ብሎ ጠራው።
16 አብራም፣ አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ ዕድሜው 86 ዓመት ነበር።