ዘፍጥረት 49 NASV

ያዕቆብ ልጆቹን ባረከ

1 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልጆቹን ሁሉ አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በኋለኛው ዘመን ምን እንደሚደርስባችሁ እነግራችሁ ዘንድ ተሰብሰቡ።

2 “እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ተሰብሰቡና ስሙ፤አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ፤

3 “ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ኀይሌና የጒብዝናዬም መጀመሪያ፤በክብር ትልቃለህ በኀይልምትበልጣለህ።

4 እንደ ውሃ የዋለልህ ነህና እልቅናአይኖርህም፤የአባትህን መኝታ ደፍረሃል፤ምንጣፌንም አርክሰሃል።

5 ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣ሰይፎቻቸው የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።

6 ወደ ሸንጎአቸው አልግባ፤ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፤በቍጣ ተነሣሥተው ሰዎችን ገድለዋል፤የበሬዎችንም ቋንጃ እንዳሻቸው ቈራርጠዋል።

7 እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።

8 “ይሁዳ፣ ወንድሞችህ ይወድሱሃል፤እጅህም የጠላቶችህን ዐንገት ዐንቆ ይይዛል፤የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይሰግዱልሃል።

9 “አንተ የአንበሳ ደቦል ይሁዳ፤ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ በምድርም ላይ ይተኛል፤እንደ እንስት አንበሳም ያደባል፤ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?

10 በትረ መንግሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤የገዥነት ምርኵዝም ከእግሮቹ መካከል።ገዥነት የሚገባው እስኪመጣ ድረስ፣ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙታል።

11 አህያውን በወይን ግንድ፣ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤ልብሱን በወይን ጠጅ፣መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።

12 ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።

13 “ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።

14 “ይሳኮር፣ ዐጥንተ ብርቱ አህያ፣በጭነት መካከል የሚተኛ፣

15 ማረፊያ ቦታው መልካም፣ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤ተገድዶም ያገለግላል።

16 “ዳን፣ ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል።

17 ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል።

18 “እግዚአብሔር ሆይ (ያህዌ)፤ ማዳንህን እጠባበቃለሁ።

19 “ጋድን ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፤እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል።

20 “አሴር ማእደ ሰፊ ይሆናል፤ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።

21 “ንፍታሌም ነጻ እንደ ተለቀቀች፣የሚያማምሩም ግልገሎችእንደምትወልድ ሚዳቋ ነው።

22 ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው።ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ።

23 ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤በጥላቻም ነደፉት።

24 ነገር ግን በያዕቆብ ኀያል አምላክ ክንድ፣እረኛው በሆነው በእስራኤል ዐለት፣ ቀስቱ ጸና፤ጠንካራ ክንዱም ቀለጠፈ።

25 አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣በሚባርክህ፣ ሁሉን ማድረግ በሚችል አምላክ፣ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣ከማሕፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።

26 ከጥንት ተራሮች በረከት፣ከዘላለም ኰረብቶች ምርቃት ይልቅ፣የአባትህ በረከት ይበልጣል፤ይኸ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ።

27 ብንያም፣ ነጣቂ ተኵላ ነው፤ያደነውን ማለዳ ይበላል፤የማረከውን ማታ ይከፋፈላል።

28 እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።

የያዕቆብ መሞት

29 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እነሆ፤ ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሶአል፤ በኬጢያዊው በኤፍሮን ዕርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤

30 ይህ በከነዓን ምድር፣ በመምሬ አጠገብ፣ በማክፌላ ዕርሻ ውስጥ ያለው ዋሻ፣ የመቃብር ቦታ እንዲሆን አብርሃም ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ ከነዕርሻ ቦታው የገዛው ነው።

31 በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤

32 እኔም ልያን የቀበርኋት እዚያው ነው። ዕርሻውና ዋሻው የተገዙት ከኬጢያውያን ላይ ነው።”

33 ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ፣ እግሮቹን በዐልጋው ላይ ሰብስቦ፣ የመጨረሻ ትንፋሹን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29 30 31 32 33 34 35 36 37 38 39 40 41 42 43 44 45 46 47 48 49 50