24 የፅብዖን ልጆች፦አያና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው።
25 የዓና ልጆች፦ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ አህሊባማ፤
26 የዲሶን ልጆች፦ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራንና ክራን፤
27 የኤጽር ልጆች፦ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤
28 የዲሳን ልጆች፦ዑፅና አራን።
29 የሖሪውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣
30 ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።