5 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን፣ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላካቸው ሠረገላዎች ላይ አወጧቸው።
6 ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብፅ ወረዱ።
7 ወደ ግብፅም የወረደው፣ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን ማለት ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው።
8 ወደ ግብፅ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ ያዕቆብ ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል።
9 የሮቤል ልጆች፦ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው።
10 የስምዖን ልጆች፦ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደውሳኡል ናቸው።
11 የሌዊ ልጆች፦ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው።