4 ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ።”
5 ኖኅም እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።
6 የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የ600 ዓመት ሰው ነበር።
7 ኖኅና ወንዶች ልጆቹ፣ ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች ከጥፋት ውሃ ለመትረፍ ወደ መርከቧ ገቡ።
8 ንጹሕ ከሆኑትና ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት፣ ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ ጥንድ ጥንድ፣
9 ተባዕትና እንስት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ኖኅን ባዘዘውም መሠረት ወደ መርከቧ ገቡ።
10 ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ።