17 ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጽሬዳ መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ።
18 እነዚህ ሰሎሞን ያሠራቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ብዙዎች ስለሆኑ የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደሆነ አልታወቀም ነበር።
19 እንደዚሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሠራ፤ እነዚህም፦የወርቅ መሠዊያ፣የገጸ ኅብስቱ ጠረጴዛ፣
20 በተሰጠው መመሪያ መሠረት፣ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት እንዲነድዱ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞች ከነቀንዲሎቻቸው፣
21 የወርቅ አበባ ቅርጽ ሥራዎች፣ ቀንዲሎችና መኮስተሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።
22 ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ የመብራት ማጥፊያዎች፣ ለመርጨት የሚያገለግሉ ጐድጓዳ ሳሕኖች፣ ጭልፋዎችና ጥናዎች፣ እንደዚሁም የቤተ መቅድሱ የወርቅ መዝጊያዎች፣ ይኸውም የቅድስተ ቅዱሳኑ የውስጠኛው መዝጊያዎችና የቤተ መቅደሱ ዋናው አዳራሽ መዝጊያዎች ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ።