3 “በአምላካችን አገልጋዮች ግንባር ላይ ማኅተም እስከምናደርግባቸው ድረስ ምድርን ወይም ባሕርን፣ ወይም ዛፎችን አትጒዱ።”
4 የታተሙትንም ቊጥር ሰማሁ፤ እነርሱም ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ፤
5 ከይሁዳ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ከሮቤል ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ከጋድ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣
6 ከአሴር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ከንፍታሌም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ከምናሴ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣
7 ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣
8 ከዛብሎን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ከዮሴፍ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፣ከብንያም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ።
9 ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በዙፋኑና በበጉ ፊት ማንም ሊቈጥራቸው የማይችል ከሕዝብ፣ ከነገድ፣ ከወገን፣ ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው፣ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው ነበር።