1 ዜና መዋዕል 15:22-28 NASV

22 የዝማሬው ኀላፊ ሌዋዊው አለቃ ክናንያ ነበረ፤ ይህን ኀላፊነት የወሰደው በዝማሬ የተካነ ስለ ነበር ነው።

23 በራክያና ሕልቃና የታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤

24 ካህናቱ ሰበኒያ፣ ኢዮሣፍጥ፣ ናትናኤል፣ ዓማሣይ፣ ዘካርያስ፣ በናያስና አልዓዛር በእግዚአብሔር ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። ዖቤድኤዶምና ይሒያ ደግሞ የታቦቱ በር ጠባቂዎች ነበሩ።

25 ስለዚህ ዳዊት የእስራኤል ሽማግሌዎችና የሻለቃው አዛዦች የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት በደስታ ለማምጣት ሄዱ።

26 የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያን እግዚአብሔር ረድቶአቸው ስለ ነበር፣ ሰባት ኮርማዎችና ሰባት አውራ በጎች ሠዉ።

27 ታቦቱን የተሸከሙት ሌዋውያን ሁሉ፣ መዘምራኑና የመዘምራኑ አለቃ ክናንያ የለበሱትን ዐይነት ከቀጭን በፍታ የተሠራ ልብስ ዳዊትም ለብሶ ነበር፤ እንዲሁም ከበፍታ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ ነበር።

28 በዚህ ሁኔታ መላው የእስራኤል ሕዝብ በሆታ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፣ ጸናጽል እየጸነጸሉ፣ መሰንቆና በገና እየደረደሩ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አመጡ።