2 ዜና መዋዕል 14:4-10 NASV

4 የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ፣ሕጉንና ትእዛዙንም እንዲፈጽሙ የይሁዳን ሕዝብ አዘዘ።

5 ከእያንዳንዱም የይሁዳ ከተሞች የማምለኪያ ኰረብታዎችንና የዕጣን መሠዊያዎችን አስወገደ፤ መንግሥቱም በእርሱ አገዛዝ ዘመን ሰላም አገኘች።

6 በምድሪቱ ሰላም ስለ ሰፈነ፣ በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ። እግዚአብሔር ዕረፍት ስለ ሰጠውም፣ በዘመኑ የተዋጋው ማንም አልነበረም።

7 እርሱም ለይሁዳ ሕዝብ እንዲህ አላቸው፤ “እነዚህን ከተሞች እንሥራ፤ ማማ፣ መዝጊያና መወርወሪያ ያላቸውን ቅጥሮች በዙሪያቸው እናብጅ። አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለ ፈለግነው ምድሪቱ አሁንም የኛው ናት፤ እኛ ፈለግነው፤ እርሱም በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጠን” እነርሱም ሠሩ፤ ተከናወነላቸውም።

8 አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የያዙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሰዎች እንዲሁም ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።

9 ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰራዊትና ሦስት መቶ ሠረገላ ይዞ በመውጣት እስከ መሪሳ ድረስ መጣባቸው።

10 አሳም ሊገጥመው ወጣ፤ መሪሳ አጠገብ ባለው በጽፋታ ሸለቆም የውጊያ ቦታ ቦታቸውን ያዙ።