7 በነገሠ በሦስተኛው ዓመት በይሁዳ ከተሞች ያስተምሩ ዘንድ ሹማምቱን ማለትም ቤን ኀይልን፣ አብድያስን፣ ዘካርያስን፣ ናትናኤልንና ሚካያን ላካቸው።
8 ከእነዚህም ጋር ጥቂት ሌዋውያን ነበሩ፤ ስማቸውም፦ ሸማያ፣ ነታንያ፣ ዝባድያ፣ አሣሄል፣ ሰሚራሞት፣ ዮናትን፣ አዶንያስ፣ ጦብያና ጦባዶንያ ነበር። ካህናቱ ደግሞ ኢሊሳማና ኢዮራም ነበሩ።
9 እነርሱም የእግዚአብሔርን የሕጉን መጽሐፍ ይዘው በመሄድ በይሁዳ ሁሉ ላለው ሕዝብ አስተማሩ፤ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በመዘዋ ወርም ሕዝቡን አስተማሩ።
10 በይሁዳ ዙሪያ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርሀት ስለወደቀባቸው ኢዮሣፍጥን አልተዋጉትም።
11 ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።
12 ኢዮሣፍጥም እያየለ ሄደ፤ በይሁዳም ምሽጎችና የዕቃ ማከማቻ ከተሞች ሠራ።
13 በይሁዳም ከተሞች እጅግ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ነበረው። ደግሞም በቂ ልምድ ያላቸውን ተዋጊዎች በኢየሩሳሌም አስቀመጠ።