1 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በደኅና በተመለሰ ጊዜ፣
2 ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፣ “አንተ ክፉውን መርዳትህና እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ማፍቀርህ ተገቢ ነውን? ስለዚህ የእግዚአብሔር ቊጣ ባንተ ላይ ነው፤
3 ይሁን እንጂ የአሼራን ዐምዶች ከምድሪቱ ስላስወገድህና እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልብህን ስላዘጋጀህ፣ መልካም ነገር ተገኝቶብሃል”።
4 ኢዮሣፍጥ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ ከቤርሳቤህ እስከ ኰረብታማው አገር እስከ ኤፍሬም ድረስ እንደ ገና በመውጣት ወደ ሕዝቡ መካከል ገብቶ ወደ አባቶቻቸው አምላክ ወደ እግዚአብሔር መለሳቸው።
5 በምድሪቱም ላይ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ዳኞችን ሾመ፤