2 ዜና መዋዕል 21:5-11 NASV

5 ኢዮሆራም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰላሳ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ስምንት ዓመት ገዛ።

6 እርሱም የአክዓብን ልጅ አግብቶ ስለ ነበር የአክዓብ ቤት እንደ አደረገው ሁሉ የእስራኤል ነገሥታት የሄዱበትን መንገድ ተከተለ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ።

7 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ካደረገው ኪዳን የተነሣ፣ የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም የሚጸና መብራት እንዲኖር ለማድረግ ተስፋ ሰጥቶ ነበርና።

8 በኢዮሆራም ዘመነ መንግሥት ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐምፆ፣ የራሱን ንጉሥ አነገሠ።

9 ስለዚህ ኢዮሆራም የጦር ሹማምቱና ሰረገላዎቹን ሁሉ ይዞ ወደዚያው ሄደ። ኤዶማውያንም እርሱንና የሰረገላ አዛዦቹን ሁሉ ከበቡ፤ እርሱ ግን በሌሊት ተነሥቶ የከበቧቸውን መታ።

10 ኤዶምም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ላይ እንደ ዐመፀ ነው።ኢዮሆራም የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለ ተወ፣ የልብና ከተማ በዚያኑ ጊዜ ዐመፀችበት።

11 ከዚህም በላይ በይሁዳ ኰረብቶች ላይ መስገጃ ስፍራዎች ሠርቶ የኢየሩሳሌም ሕዝብ በዚያ እንዲያመነዝር አደረገ፤ ይሁዳንም አሳተ።